የኢትዮጵያ  ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን የማበረታቻ ሽልማት እንደሚበረከትለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

ፌዴሬሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው ፥ የፊታችን ሀሙስ የዋልያዎቹ አባላት  ሽልማቱን  ይቀበላሉ ።

በሸራተን አዲስ በሚካሄድ  ስነ ስርዓት ለብሄራዊ  ቡድኑ የሚሰጠው ሽልማት የተዘጋጀው  በፌዴሬሽኑ ነው ።

ሽልማቱም የኢትዮጵያ  እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ከማዕከላዊ አፍሪካ  ሪፐብሊክ  አቻው ጋር ለመጫወት ወደ ኮንጎ ብራዛቪል ከማቅናቱ በፊት ቃል የተገባለት ነው ተብሏል ።

 

በዘርዓይ እያሱ