አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የጌታነህ ከበደ ከእሁዱ ጨዋታ ውጪ መሆን ያልጠበቁት እና ያሳዘናቸው መሆኑን ተናገሩ ።

ያሉት ቀሪ ተጫዋቾች ውጤት መቀየር የሚችሉ መሆናቸውን ነው ለሱፐር ስፖርት የገለጹት።

አሰልጣኙ ጌታነህ ፈጥኖ እንደሚያገግም ተስፋ አለኝ  ፥ ተጨዋቾቼም እንደ ቡድን የአፍሪካ ሻምፒዮኖቹን ማቆም የሚችሉ ናቸው ብለዋል።

በተጨዋቾቹ ላይ የድካም ስሜት እንዳይፈጠርም በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ልምምድ በማድረግ ላይ እንደሚገኙም ነው ያስረዱት።

ከጌታነህ ጉዳት በስተቀር ቀሪ ተጫዋቾች በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም አሰልጣኝ ሰውነት አስታውቀዋል።

 

Source: Supersport.com