አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 400 መንገደኞችን ማሳፈር የሚችል ዘመናዊ ቦይንግ አውሮፕላን በመጪው ሳምንት ሊረከብ ነው።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም እንደተናገሩት  ፥ አውሮፕላኑ  ነዳጅ ቆጣቢና ረዠም ርቀት መጓዝ የሚችል ነው።

አውሮፕላኑ  ወደ ቻይናና አሜሪካ የሚደረጉ በረራዎችን በተቀላጠፈ መልኩ ማስኬድ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ከያዝነው ወር መጨረሻ ጀምሮ በሳምንት ሶስት ጊዜ ወደ ሉዋንዳና ዋሽንግተን ዲሲ የሚደረጉ በረራዎች በአዲሱ አውሮፕላኖች የሚደረጉ መሆናቸውም ታውቋል።

በመጪው ሳምንት እንደሚገባ የሚጠበቀው ይህ አውሮፕላን ፥ አየር መንገዱ ከቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት ካዘዛቸው አራት አውሮፕላኖች መካከል አንዱ ነው።